Amharic (Am)English (United Kingdom)

Cultural Foods

  • ayeb.png
  • doro wote.png
  • gomen-besega.png
  • gomen.png
  • kitifo.png
  • shiro-wote.png
  • tibse.png

ምግብና መጠጥ

ሰፊና በግሩም ሁኔታ የተደራጀው የማብሰያ ክፍል ውስጥ፤ በታታሪ ባለሙያ የምግብ አብሳዮች የሚዘጋጀው ጣፋጭ የባህል ምግብ፤ በኢትዮጵያ ባህላዊ አቀራረብ ለደንበኞች ይቀርባል፡፡ ለጎብኝዎችና ለእንግዶች፤ ይህንን ጣት የሚያስቆረጥም ምግብ በኢትዮጵያዊ አመጋገብ ስርዓት መሰረት ጣቶችን በመጠቀም መመገብ ግድ ይላል፡፡ ዩድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ፤ አትክልት፤ ስጋና የስጋ ውጤቶችን አካተው የሚዘጋጁትን ምግቦችን ጨምሮ፤ ከ38 ዓይነት በላይ ባሕላዊ ምግቦችን በጥራት ያዘጋጃል፡፡ የፍስክ ምግቦች፤ የተለያዩ የወጥ አይነቶች፤ የበሬ እና የበግ ሥጋ ጥብስ፣ የዶሮ ወጥ፣ ክትፎ እና ሌሎች ከእንጀራ፤ ቆጮና ዳቦ ጋር የሚቀርቡ ሲሆን፤ ዮድ አቢሲንያን የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች ለማጣጣም ለሚፈልግ ሁሉ ተመራጭ የምግብ አዳራሽ ያደርገዋል፡፡

 

ዮድ አቢሲንያ ለምግቦቹ ማጣፈጫ ታዋቂ ከሆነው ንፁህ የሸኖ ቅቤ የሚያዘጋጅ ሲሆን፤ ለምግቡም ማባያነት የሚቀርበው ቅመማ ቅመምና ሚጥሚጣም በባህሉ መሰረት በጥንቃቄ ይዘጋጃል፡፡ በምግብ ቤት ውስጥ የሚቀርቡ ኢትዮጵያዊ ጣዕም ያላቸው ምግቦች በዛ ያሉ ሲሆኑ፤ አንድ በያይነቱ፤ አይብ፣ ስልጆ ልዩ ልዩ እንደጐመን ካሉ አትክልት፤ ከበሬ፤ ከበግና ከዶሮ ስጋ የተሰሩ የቀይ፤ አልጫና ሌሎች የወጥ አይነቶችን የያዘና መጠኑም የአንድን ተመጋቢ ፍላጎት በሚገባ የሚያሟላ ነው፡፡

 

ዮድ የብርቱካን፣ የቡና የሎሚና ሌሎች 12 ዓይነት ጣዕም ያላቸውን የባህል አረቄ መጠጦችን ያቀርባል፡፡ ጠጅ ደግሞ ከንፁህ ማር ተሠርቶ በሁለት አይነት፤ የበሰለና ለጋ ጠጅ ተብሎ፤ በባህላዊው ብርሌ ለእንግዳ ይቀርባል፡፡ በርካታ የባህል አዳራሹ ታዳሚዎችም አንድ ብርሌ ጠጅ ከቀመሱ በኋላ በመድረኩ ላይ ወጥተው ባህላዊ ሙዝዋዜውን ያስነኩታል፡፡ ምዕራባውን የፆም በያይነቱና የስጋ ጥብሶችን ሲያዘወትሩ፤ ከምሥራቅ የሚመጡ እንግዶች ከከብት ጨጓራ የሚሰራውንና “ትሪፓ” የሚባለውን ጣፋጭ ምግብን ይወዳሉ፡፡ አፍሪካውያን ግን ሁሉንም የምግብ ዓይነቶች ሳይመርጡ ያጣጥማሉ፡፡

 

አስተናጋጆቹ በኢትዮጵያ የባሕል ልብስ አጊጠው፤ ሰርክ በኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት ፈገግታ ተላብሰው፤ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ከእንሰሳት ቆዳ የተሰራውና በሚገባ ዲዛይን የተደረገው ሜኑ፤ በውስጡ 40 የሚጠጉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችንና ከ45 የላነሱ የመጠጥ ዝርዝሮችን ይዟል፡፡

 

በምግብ አዳራሹ በስተቀኝ በኩል፤ የኢትዮጵያን ባሕላዊ የቡና ጀበና የሚያሳይ ምስል ይገኛል፡፡ ከስሩም አንዲት ወጣት ሴት ዘወትር ምሽት፤ ጣፋጭ ቡና እያፈላች ኢትዮጵያዊ ባህልን በሚያንፀባርቅ የቡና አፈላልና አቀራረብ፤ የዮድ እንግዶችን ታስተናግዳለች፡፡ በዚህ አስደናቂ ባሕላዊ የቡና አፈላል ሥርዓት፤ ቡናው ታጥቦ፣ ተቆልቶ መዓዛው አየሩን ሲያውደው፤ ከዚያም የተወቀጠው ቡና ተፈልቶ፤ ከለምለም ቀጤማውና ዕጣኑ ሽታ ጋር ተዋህዶ፤ ቡናው ከፈንዲሻ ጋር ለእንግዶች ሲቀርብ ልዩ ትዕይንት ይፈጥራል፡፡